የምወዳደርበት ምክንያት

ቀጣይዋ የዲሲ ምክር ቤት ሊቀመንበር ለመሆን የምወዳደርበት ምክንያት አሁን ከማናቸውም ጊዜ ይልቅ በመላው ዲሲ ለእያንዳንዱ ሰው እና ቤተሰብ የሚሰራ አመራር ስለሚያስፈልገን ነው፡፡ መንግሥት የዛሬዎቹን ተግዳሮቶች ፊት ለፊት እንዲገጥም እና ለተሻለ ነገ የሚያስፈልግ መሠረተ ልማት እንዲገነባ ሪፎርም ለማምጣት ቁርጠኛ አቋም አለኝ፡፡ መንግሥት ሁሉንም ነዋሪዎች እንዲያገለግል እና ዲሲን ይበልጥ ጠንካራ እንዲያደርግ ለዓመታት ለሥነ ምግባር እና የተሻለ ተጠያቂነት ስታገል ያካበትኩትን ልምድ ወደ ዊልሰን ሕንጻ አመጣለሁ፡፡ በአዳዲስ ሃሳቦች፣ በትብብር አመራር እና ጠንካራ እሴቶች እያንዳንዱ የዋሽንግተን ነዋሪ ብሩህ የወደፊት ጊዜ እንደሚኖረው ማረጋገጥ እንችላለን፡፡

የቤተሰቤ፣ የጓደኞቼ እና የጎረቤቶቼ ድጋፍ እና ፍቅር ባይኖረኝ ኖሮ ለሊቀመንበርነት ለመወዳደር አልነሳሳም ነበር፡፡ በዚህ ውድድር ውስጥ ያለሁት በእነርሱ ምክንያት እና ለእነርሱ ነው፡፡

ብሩህ እና ሁኔታዎች እንደአግባብነታቸው የሚስተናገዱባት ከተማ

የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከማጋጠሙ በፊት፣ በቤተሰቤ ውስጥ አነስተኛ ነገሮች እንኳን ከመንገዳችን ሊያወጡን ይችላሉ በሚል ግንዛቤ በትምህርት ቤት፣ በሥራ እና በዕለት ተዕለት እንቅስቃሴዎቻችን ላይ ሚዛናዊነት እንዲኖር አድርገናል፡፡ወረርሽኙ አዳዲስ ተግዳሮቶች ከማምጣቱም በተጨማሪ በሕዝብ ጤና ጥረቶች፣ ውጤቶች፣ መሠረታዊ ፍላጎቶች እና የኢኮኖሚ መሻሻል ላይ አስደንጋጭ ክፍተቶች አምጥቷል፡፡ በዲሲ እና አገራችን የሚገጥመን ችግር ኮቨድ-19 ብቻ አይደለም፡፡ የአየር ንብረት ለውጥም እንዲሁ የጋራ የወደፊት ሕይወታችን ላይ ስጋትን የሚፈጠር ሲሆን፣ ተጠቃሚ ባልሆኑ ማኅበረሰቦች ላይ የሚያስከትለው ተጽዕኖ ደግሞ ከፍተኛ ነው፡፡

አድሪያን በ2016 የዳኮታ አክሰስ ፓይፕላይን ተቃውሞ ላይ በዩናይትድ ስቴትስ ካፒቶል ፊት ለፊት

አስፈላጊ የሆኑ ደጋፊ እና አዳዲስ መሠረተ ልማቶች መገንባት እንችላለን፣ መገንባትም አለብን፡፡ ለመፈጸም ለሚቻለው ሁሉ ተጋት፣ ቁርጠኝነት እና ራዕይ ወሳኝ ናቸው፡፡ ለልጆቼ፣ ለእናንተ ልጆች እና ለቤተሰቦቻችን፣ ለማኅበረሰቦቻችን እና ለወደፊት ትውልዶች እነዚህን ተግዳሮቶች ለመጋፈጥ ዝግጁ ነኝ፡፡

ሥነ ምግባር ያለው መንግሥት

በበርካታ ዓመታት ሂደት፣ የቀድሞ ዋርድ 2 የምክር ቤት አባል የነበሩት ኤቫንስ የተሳተፉበት የሥነ ምግባር ቅሌት እየተገለጠ ሲሄድ አይቻለሁ፤ ይህም የአካባቢ መንግሥታትን በአንድ ቋት ከትቶ የመመልከትን አብዛኛዎቹን አዝማሚያዎች አረጋግጧል፡፡ በመላው ዲሲ ከአድቫይዘሪ ኔበርሁድ ኮሚሽነሮች ጋር የሰራሁ ሲሆን፣ የሲዲ ምክር ቤት ትክክለኛ እርምጃ እንዲወሰድ ከጠየቁት ተመራጭ ባለሥልጣናት መካከል ከመጀመሪያዎቹ አንዷ ነኝ፤ በዚህም ምክንት ኤቫንስ በገዛ ፈቃዳቸው ሥልጣናቸውን ለቅቀዋል፡፡ ነገር ግን ይህ ሙስናቸው ሕዝቡ ተጠያቂነት እንዲሰፍን ድምጹን አውጥቶ እስኪጠይቅ ድረስ ለምን ለረጅም ጊዜ ቆየ? የእኛ ምክር ቤት አመራር ለአባላቱ ከፍተኛ ስታንዳርድ ሊኖረው አይገባምን?

ጃቪ፣ ኤሪን፣ አድሪያን፣ ማቴዮ እና ኤሪክ በ2017 የአካባቢ ምርጫ የሕዝብ የገንዘብ እገዛን በመደገፍ

ጥሩ አስተዳደር ቀጣይነት ያለውን ክትትል ይጠይቃል፡፡ ገለልተኛ፣ አስቀድሞ መፍትሔ የሚሻ እና ከአባላቱ ተጠያቂነትን የሚጠይቅ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ይህንን የማድረግ ልምዱ አለኝ፤ ለተሻለ እና ይበልጥ ሥነ ምግባር ለተሞላ መንግሥት ቁርጠኝነት አለኝ፡፡ በዚህም ምክንያት ውድድሬን በፍትሐዊ ምርጫ ፕሮግራም አማካኝነት ለማካሄድ ወስኛለሁ፡፡ የምርጫ ውድድራችን ታማኝነቱ ለማኅበረሰባችን እንጂ ለትልልቅ የንግድ ድርጅቶች እና ሎቢስቶች አይሆንም፡፡ የሕዝብ ፋይናንስ እገዛ ለዚህ የምርጫ ውድድር እና ለነዋሪዎች ለሠራተኛ ነዋሪዎች እና ለቤተሰቦች ለውጦች እንዲመጡ ለመከራከር እውነተኛ ሥልጣን ይሰጣል፡፡

ፍትሐዊ፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው የመንግሥት አገልግሎቶች በዲሲ

አድቫይዘሪ የኔበርሁድ ኮሚሽነር እንደመሆኔ መጠን፣ በሌሉ የማቆሚያ ምልክቶች፣ ባረጁ የእግረኛ መንገዶች፣ በማርጀት ላይ ባሉ የትምህርት ቤት ሕንጻዎች እና በሌሉ የሕዘብ ትራንስፖርት ጉዳዮች ላይ በመላው ዲሲ ከሌሎች ኮሚሽነሮች እና ነዋሪዎች ጋር አብሬ ሰርቻለሁ፡፡ በልዩ ልዩ የመኖሪያ አካባቢዎች ችግሮች ተመሳሳይ ቢሆኑም እንኳን፣ መንግሥት ለችግሮቹ የሚሰጣቸው መፍትሔዎች ተመሳሳይ አይደሉም፡፡ የሚኖሩት በየትም ቢሆን፣ እነዚህ ችግሮች ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

አድሪያን በታኮማ ሜትሮ ስቴሽን በ#TranspoBINGO ብስክሌቱን በሜትሮባስ ላይ እየጫነ

መንግሥት ለሁሉም ነዋሪዎች ከፍተኛ ጥራት ያለው፣ አስተማማኝ እና ወጥነት ያላቸውን አገልግሎቶች ለሁሉም ነዋሪዎች ሊሰጥ ይገባል፡፡ ክትትል እና ተጠያቂት ወሳኝ ናቸው፣ እኔም በየዕለቱ ክትትል አደርጋለሁ፤ ዓይኖቼን የአጭር ጊዜ ችግሮች ላይ በመትከል ብቻ ሳይሆን ሥርዓታዊ ተግዳሮቶችን በመለየት እና መፍትሔዎችን በማቅረብ እንዲሁም ተግባራዊ በማድረግ እሰራለሁ፡፡