ስኬታማ ቤተሰቦች

በሁሉም የዕድሜ ደረጃዎች ላይ የሚገኙ የዲሲ ነዋሪዎች መመንደግ ይገባቸዋል፡፡ ነገር ግን ከተማችን አሁንም ቤተሰቦችን ወደ ኋላ እየተወች ትገኛለች፡፡ ከመላው አገሪቱ የጥቁር እናቶች በወሊድ ምክንያት የሚከሰት ሞት ከፍተኛው ቁጥር የሚመዘገበው በዲሲ ነው፡፡ ቤተሰቦች የሕጻናት እንክብካቤ መስጫዎች ማግኘት ያስቸግራቸዋል፤ ለልጆቻቸው ትምህርት ቤት ለማግኘት ደግሞ ዕጣ ማውጣት አለባቸው፡፡ በዚህም ምክንያት በመሠረቱ በእርግጠኝነት ሊገኙ ይገባቸው የነበሩ ጥራት፣ የሕጻናት እንክብካቤ በተመጣጣኝ ዋጋ፣ ጥሩ የመኖሪያ አካባቢ ትምህርት ቤት እና ተደራሽ የድኅረ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በተመጣጣኝ ዋጋ በዕድል እጅ እንዲወድቁ ይደረጋል፡፡ የምግብ እና የመኖሪያ ዋስትና እጦት እየጨመረ ሄዷል፤ ይህም ልጆች እና አዛውንቶች ተጋላጭ እንደሆኑ አድርጓል፡፡ የሦስት በሕዝብ ቻርተርት ትምህርት ቤት የሚማሩ ልጆች ወላጅ እና ሠራተኛ እንደመሆናቸው ኤሪን ለቤተሰብ ቅድሚያ መስጠት አስፈላጊ እንደሆነ ያምናሉ፡፡

Erin will support ongoing efforts for a birthing center and improved access to medical services east of the Anacostia River. She will fight for high-quality education in every part of our city by making sure at-risk funds are used to support at-risk families, and not to substitute for basic needs, and all schools have librarians and language, music, and arts teachers. Government should have a holistic view of childhood development and education, and Erin will work to ensure that all students receive social, emotional, and mental health services, that their special education needs are met, that all our students feel represented and supported no matter their sexual orientation or gender identity, and that they can get to and from school safely every day. Erin believes residents deserve to age in place and with dignity, which requires flexibility for accessory dwellings and other affordable housing and robust and accessible public transportation networks that allow residents to stay connected to family, friends, and community. 

በኮቪድ-19 ወረርሺኝ ጊዜ ቤተሰቦች ተገቢው ትኩረት የተሰጣቸው አይመስልም፡፡ በከፊል ውስብስብ እና ተደራሽ ባልሆኑ የኦንላይን ማመልከቻዎች ምክንያት አረጋዊያን ክትባት እና የኪራይ እንዲሁም የአገልግሎቶች እገዛ ፕሮግራም ሊያገኙ አልቻሉም፡፡ አሁን በአዲስ የኮቪድ-19 ወረርሺኝ ምክንያት ወላጆች በትምህርት ቤት ውስጥ የልጆቻቸው ደህንነት ያሳስባቸዋል፡፡ የትምህርት ቤቶች እና የቤተሰቦች አስተውሎት የሞላበት ድጋፍ በሌለበት ሁኔታ ባለፈው ዓመት የጠፋውን የትምህርት ጊዜ ማካካስ አይሳካም፡፡ በቅርብ ታሪካችን ካጋጠመን ከፍተኛው ከትምህርት ጋር በተያያዘ ቀውስ፣ የወቅቱ ሊቀመንበር የምክር ቤቱን የትምህርት ኮሚቴ በተኑ፣ ይህም እጅግ ወሳኝ በሆነ ሰዓት ቁጥጥር፣ ተጠያቂነት እና አጠቃላይ ዕቅድ የመንደፍ ችሎታን አዳክሟል፡፡ ኤሪን ቤተሰብን መደገፍ ብዙ ጥረት የሚጠይቅ መሆኑን ያውቃሉ፤ ሊቀመንበር እንደመሆናቸው መጠን፣ ዓይነት እና ዕድሜ ከግምት ሳይገባ ለዲሲ ቤተሰብ ቅድሚያ የሚሰጥ መንግሥት ይመራሉ፡፡

የኤሪን ተሞክሮ ፡-

በዓመታቱ ሂደት፣ ኤሪን የቤተሰብ ፈቃድ ከክፍያ ጋር እንዲፈቀድ እና የሕጻንነት ዘመን ትምህርት እንዲኖር ታግለዋል፤ ወላጆች ልጆቻቸውን ወይም ታማሚ ዘመዶቻውን መንከባከብ እንዲችሉ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጥ፣ ከፍተኛ ጥራት ያለው የሕጻናት እንክብካቤ በተመጣጣኝ ዋጋ አማራጮች እንዲኖሩ ታግለዋል፡፡ የአድቫይዘሪ ኔበርሁድ ኮሚሽነር አንደመሆናቸው መጠን የትምህርት ቤት ፈንድ፣ ዕቅድ እና መልሶ መከፈት በተመለከተ ተጠያቂነት እና ግልጽነት እንዲኖር አጥብቀው ይጠይቃሉ፡፡ ለልጆች በሲቪክ ትምህርት፣ ለቤተሰብ ተስማሚ በሆኑ የማኅበረሰብ አገልግሎት ዝግጅቶች እና ለአካባቢ የአዛውንቶች አካባቢ ድጋፍ በመስጠት ቤተሰቦችን ለመደገፍ እና ለማሳተፍ ጊዜ ይሰጣሉ፡፡