ኤሪን ይተዋወቁ

ኤሪን ፓልመር እባላለሁ፤ የሦስት ብሩካን ልጆች እናት ነኝ፤ የሥነ ምግባር ጠበቃ ስሆን፣ ራሴን ለሕዝብ አገልግሎት የሰጠሁ ሰው ነኝ፡፡ ከሞላ ጎደል ከሁለት አስርተ ዓመታት በፊት ወደ ዲሲ ከተዘዋወርኩ ጊዜ ጀምሮ፣ በፌዴራል እና በአካባቢ መንግሥታት ዘንድ የሥራ ቦታ ጥበቃዎችን በማስፋፋት ስሰራ እና ለግልጽነት እና ተጠያቂነት ስታገል ቆይቻለሁ፡፡ በዋርድ 4 አድቫይዘሪ ኔበርሁድ ኮሚሽነር እንደመሆኔ መጠን ፣ በዕለት ተዕለት ኑሯችን ላይ ተጽዕኖ ስላላቸው ጉዳዮች ማለትም እንደ ትራፊክ ደህንነት፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ትምህርት ቤቶች፣ እና የተሻለ የሕዝብ ትራንስፖርት በተመለከተ ከጎረቤቶቼ ጋር በመሆን እታገላለሁ፡፡ ወደ ዲሲ ምክር ቤት አዲስ ኃይል እና ራዕይ ለማምጣት ለሊቀመንበር ወንበር በመወዳደር ላይ ነኝ፡፡

በዲሲ የቤተሰብ ምስረታ

ዲሲ እንዲሁ የምኖርበት ቦታ ብቻ አይደለም ፡- እኔ እና ባለቤቱ ቤታችንን ለመገንባት እና የቤተሰባችንን መሠረት ለመጣል የወሰንነው በዚህ ነበር፡፡ የወጣትነት የዕድሜ ዘመኔን ያሳለፍኩት ከአንድ የመኖሪያ ቦታ ወደ ሌላ በመዘዋር ሲሆን፣ ያደግሁት በካሊፎርኒያ እና ኮሎራዶ ነበር፡፡ በኋላ፣ በፔንሲልቫኒያ ዩኒቨርሲቲ ገባሁ እንዲሁም በሳንቲያጎ፣ ቺሌ ተምሬያለሁ፡፡ በአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት እና የምረቃ ትምህርት ቤት ለመማር ወደ ዲሲ ስመጣ፣ ለመጀመሪያ ጊዜ የእኔ ቦታ እዚህ ነው የሚል ስሜት ተሰማኝ፡፡

.

አሪን ከባለቤታቸው ኤሪክ እና ከሦስት ልጆቻቸው ጋር፡- አድሪያን (10)፣ ማቴዎ (8) እና ጃቪየር (6)፡፡

የምወዳደርበት ምክንያት

የሕግ ትምህርት ቤት ትምህርቴን ካጠናቀቅሁ እና የምረቃ ዲግሪዬን ካገኘሁ በኋላ፣ በዲሲ የይግባኝ ፍርድ ቤት ሬጅስትራር በመሆን ሰራሁ፤ ባለቤቱን ያገኘሁት በዚያው ነበር፤ እርሱም በፍርድ ቤቱ በሬጅስትራርነት ይሰራ ነበር፡፡ ስለ ዲሲ ሕግጋት በመማር ላይ ሳለን እና ስለከተማዋ ስናውቅ በፍቅር ወደቅን፡፡ ተጋባን፣ በታኮማ መኖር ጀመርን፣ ሦስት ልጆችም ወለድን፡- አድሪያን (10)፣ ማቴዮ (8) እና ጃቪየር (6)፡፡ ልጆቻችን እንደ ቤተሰብ ታላቅ ዋጋ የምንሰጣቸውን እሴቶች ያለማቋረጥ ያስታውሱናል፣ እነርሱም፡- ደግነት፣ ሃዘኔታ እና ማኅበረሰብን ማገልገል ናቸው፡፡

ኤሪን እና ኤሪክ በሞሪሰን-ክላርክ ሂስቶሪክ ኢን ኤንድ ሬስቶራንት የጋብቻ በዓላቸውን ሲያከብሩ

ወደ ሆስፒታል በመሄድ ላይ ሳሉ ጃቪ ከተወለደ በኋላ ኤሪን፣ ኤሪክ እና ጃቪ

እያንዳንዱ ልደት አስገራሚ ነገሮች እና ፈተናዎች ይዞ መጥቷል፣ ነገር ግን የጃቪ ልዩ ትውስታ ያለው ነው፡፡ ወደ ሆስፒታል በመሄድ ላይ ሳለን በ13th Street and Gallatin Street, NW በእህቴ መኪና የኋላ ወንበር ለመወለድ ደረሰ፡፡ ከመጀመሪያው እስትንፋሱ ጀምሮ የማኅበረሰባችን አካል ሆኖ ቆይቷል፡፡

ለተሻለ እና ይበልጥ ተጠያቂ ለሆነ መንግሥት በመታገል ላይ

በሙያዬ መሥራት ከጀመርኩበት ጊዜ ጀምሮ መንግሥትን ተጠያቂ ለማድረግ ሰርቻለሁ፤

በፍርድ ቤት በሬጅስትራርነት ከሰራሁ በኋላ፣ በአንድ የሕግ መሥሪያ ቤት ሰርቻለሁ፤ አብዛኛውን ጊዜዬን ያሳለፍኩት ደግሞ ነጻ የሕግ አገልግሎት በመስጠት ነው፡፡ ከእነዚህም መካከል በፖለቲካ እምነት ምክንያት በመንግሥት የሚፈጸምን የኃይል ድርጊት በመሸሽ ላይ ለነበረ ሰው የፖለቲካ ጥገኝነት አስገኝቻለሁ፣ የአካል ጉዳት ያለበት ልጅ በትምህርት ቤት ሊያገኝ የሚገባውን አገልግሎት ማግኘቱን ለማረጋገጥ ወክዬዋለሁ፤ ለወጣት ጥፋተኞች ያለ አመክሮ የዕድሜ ልክ እስራትን ለማስቀረት ስለወጣቶች የአዕምሮ ዕድገት ሳይንስ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት መግለጫዎች አቅርቤያለሁ፡፡

ኤሪን በ2017 የእናቶች ሞት መርማሪ ኮሚቴ እንዲቋቋም በዲሲ ምክር ቤት ምሥክርነት ሲሰጡ

ላለፉት ሰባት ዓመታት በፌዴራል ፍርድ ቤት የሥነ ምግባር ጠበቃ በመሆን አገልግያለሁ፡፡ በዚያም ስፔሻላይዝ ያደረግሁት በሥራ ቦታ ተጠያቂነት ላይ ነበር፡፡ በአንድ ወቅት የወሲብ ጥቃት እና ትንኮሳ ተጠቂ የነበርኩ እንደሆኔ መጠን፣ እነዚህ መዋቅራዊ ተግዳሮቶች ደንቦች እና ሕግጋትን መከለስ ጉዳይ ብቻ ሳይሆኑ፣ ይልቁንም በሥራ ቦታዎች የደህንነትን ትርጓሜ የመከለስን የሞራል ጥያቄ የሚያስነሱ ናቸው፡፡ በመንግሥት ውስጥ የሥልጣን ሚዛናዊነትን ለማምጣት አስፈላጊ በሆነ ተቋም ውስጥ ተጠያቂነትን እና የሥራ ቦታ ጥበቃን ለማሻሻል በሰራሁት ሥራ ኩራት ይሰማኛል፡፡

ኤሪን በአድቫይዘሪ ኔበርሁድ ኮሚሽን የ4B ስብሰባ ላይ፡፡

ከ2018 ጀምሮ በምርጫ በሚያዝ የአካባቢ ከፍተኛ የኃላፊነት ቦታ ላይ አድቫይዘሪ ኔበርሁድ ኮሚሽነር በመሆን አገልግያለሁ፡፡ በችግሮች ላይ ብቻ በማተኮር ሳይሆን ሥርዓታዊ ችግሮች ላይ ትኩረት በማድረግ እና በመላው ዲሲ መንግሥትን ለማሻሻል የሚያስችሉ መፍትሄዎች በመለየት የትራፊክ ደህንነት፣ የመሠረተ ልማት፣ የመኖሪያ ቤት፣ የትምህርት እና የማኅበረሰብ ደህንነት ችግሮችን ለመፍታት ሰርቻለሁ፡፡ ኮሚሽነር እንደመሆኔ መጠን መለያዬ በአካባቢዬ አፋጣኝ ፍላጎቶች ላይ ማተኮር ብቻ ሳይሆን እያንዳንዱን የመኖሪያ አካባቢ የተሻለ ለማድረግ በመላው ዲስትሪክት አጋርነቶችን መገንባት ጭምር ነው፡፡

በማደግ ላይ ያለ ማኅበረሰብ

ማኅበረሰብ የጥንካሬያችን የማዕዘን ድንጋይ ነው፡፡ ወሳኝ ከምላቸው እሴቶች መካከል አንዱ ከሰዎች ጋር የሃሳብ ልውውጥ ማድረግ እና ግንኙነቶችን መመስረት ነው፡፡

እንደ ቤተሰብ አንዳንድ መሠረታዊ ደንቦች አሉን፡- በእያንዳንዱ ቀን ከቤት ውጪ አንዳንድ ሥራዎች እንሰራለን፣ ለመማር አንዳች ነገር እናደርጋለን እንዲሁም ማኅበረሰቡን ለመደገፍ አንድን ነገር እናደርጋለን፡፡ ልጆቼ በታኮማ የመኖሪያ አካባቢያችን ጽዳት ላይ በመደበኛነት ይሳተፋሉ፣ በሙቹዋል ኤይድ ላይ በበጎ ፈቃደኝነት ይሳተፋሉ እንዲሁም በማኅረሰብ ስብሰባዎች ላይ ይሳተፋሉ፡፡ በሲቪክ ተሳተፎ እና በማኅበረሰብ አገልግሎት ለልጆች በርካታ ዝግጅቶች እናካሂዳለን፤ ከእነርሱም መካከል በዲሲ ምክር ቤት የሎቢ ቀን ይካተታል!

ኤሪን በ2018 ዓመታዊ የኬኔዲ ስትሪት ፌስቲቫል ላይ የዕደ ጥበባት ጠረጴዛ ላይ ሲሰሩ፡፡

ማቴዮ እና አድሪያን በ2017 የዲሲ ምክር ቤት ከወቅቱ የምክር ቤት አባል ብራንደን ቶድ ጋር የሃሳብ ልውውጥ ሲያደርጉ፡፡

ኤሪን፣ አድሪያን እና ማቴዮ እና በርካታ ልጆች በ2017 በዲሲ ምክር ቤት ከምክር ቤት አባል አሊሳ ሲልቨርማን ጋር፡፡

ለከተማችን መልሰው አስተዋጽዕዖ በሚያደርጉ በበርካታ የማኅበረሰብ ድርጅቶች ውስጥ መሪ ሆኜ ስሳተፍ ነበር፤ በአሁኑ ጊዜ በኦልድ ታኮማ ቢዝነስ ማኅበር ውስጥ የቦርድ አባል ሆኜ በማገልገል ላይ እገኛለሁ፡፡ ከዚህ ቀደም በማኖር ፓርክ የዜጎች ማኅበር ውስጥ በጸሐፊነት፣ በኬኔዲ ስትሪት የልማት ኮርፖሬሽን ውስጥ በቦርድ አባልነት፣ የኮሌጅ ትምህርታቸውን መልሰው ማኅበረሰባቸውን ለማገልገል ለሚያውሉ በዲሲ አካባቢ ለተማሪዎች ነጻ የትምህርት ዕድል በሚሰጠው የተማሪዎች ትምህርት እና ሊደርሺፕ ፈንድ ውስጥ በቦርድ አባልነት አገልግያለሁ፡፡

ስለሙያዊ እና የበጎ ፈቃድ ልምድ ተጨማሪ መረጃ ይፈልጉ፡- 

  • አድቫይዘሪ ኔበርሁድ ኮሚሽነር፣ የነጠላ አባል ዲስትሪክት   4B02 (ወቅታዊ)
  • ኦልድ ታኮማ ቢዝነስ ማኅበር (ዋና መንገድ ታኮማ)፣ የቦርድ አባል (የወቅቱ)
  • ANC ቪዥን ዚሮ ካውከስ፣ ዋሸንግተን አካባቢ የባይሳይክሊስት ማኅበር ተባባሪ ምክትል ሊቀመንበር (የወቅቱ)
  • የዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤቶች የአስተዳደር መሥሪያ ቤት፣ ረዳት ዋና ካውንስል ክሊፎርድ ቻንስ LLP፣ ተባባሪ
  • ቤከር፣ ዶኔልሰን፣ ቢርማን፣ ክላድዌል እና በርኮዊትዝ፣ PC፣ የሕግ ሬጅስትራር፣ የአሜሪካ ዩኒቨርሲቲ የዋሽንግተን የሕግ ኮሌጅ፣ ተቆጣጣሪ ጠበቃ፣ UNROW የሰብዓዊ መብቶች ተጽዕኖ  ክርክር ክሊኒክ
  • የኮሉምቢያ ዲስትሪክት የይግባኝ ፍርድ ቤት፣ የፍርድ ቤት ሬጅስትር፣ በማኖር ፓርክ የዜጎች ማኅበር ከፍተኛ ዳኞች፣ ጸሐፊ
  • የኬኔዲ ስትሪት የልማት ኮርፖሬሽን፣ የተማሪዎች ትምህርት እና አመራር ፈንድ የቦርድ አባል
  • አሜሪካን ዩኒቨርሲቲ የዓለም ዓቀፍ አገልግሎት ትምህርት ቤት፣ ድኅረ ምረቃ ዲግሪ፣ ዓለም ዓቀፍ ሰላም እና የግጭቶች አፈታት
  • ዓለም ዓቀፍ ዩኒቨርሲቲ ዋሽንግተን የሕግ ኮሌጅ፣ ጁሪስ ዶክተር፣ ከም ሉዴ ዩኒቨርሲቲ ኦፍ ፔንሲልቫኒያ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ፣ ከም ላውዴ