ጉዳዮች

የምርጫ ቅስቀሳችን ትኩረት የሚያደርግባቸው ጉዳዮች፡- solving challenges with new energy and vision, ensuring responsive and accountable DC government, and building a DC that works for every person and family.

ሥነ ምግባር ያለው እና ተጠያቂ መንግሥት

ከኮርፖሬት የገንዘብ ረጂዎች ጋር ግንኙነት የሌላቸው የልጆች እናት ኤሪን ለረጅም ጊዜ በሥልጣን ላይ ከቆዩት እና የተለያየ ፍላጎት ካላቸው ቡድኖች በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ማሰባሰብ ከቻሉት ባላንጣቸው ጋር ለመወዳደር የሚችሉት በማቺንግ ፈንድስ አማካኝት ነው፡፡ የዲሲ መደበኛ ነዋሪዎች ድምጻቸው መሰማት እንዲችል ዕድል እንዲያገኙ በማለት ነበር ፌር ኢሌክሽን (ፍትሐዊ ምርጫ) ፕሮግራም እንዲጸድቅ ድጋፍ ያደረጉት፡፡

የማኅበረሰብ ደህንነት

በማኅበረሰቦቻችን ውስጥ የኃይል ድርጊትን ማስቀረት በቀላሉ የሚፈታ ችግር አይደለም፡፡ በብሔራዊ ደረጃ ቅድሚያ ከሚሰጣቸው እና ምርጥ ተሞክሮዎች ጋር በተጣጣመ መልኩ፣ ኤሪን የኃይል ድርጊትን በማስቀረት ላይ አበክረው ለመሥራት እና የኃይል ድርጊትን እና የሚያስከትለውን አሉታዊ ተጽዕኖ ለመቀነስ ጠንካራ ማኅበረሰቦች ለመገንባት ቁርጠኛ ናቸው፡፡

ዘመናዊ መንግሥት

ኤሪን ዘመናዊ፣ በሚገባ የሚሰራ ለመንግሥት ፕሮግራሞች፣ ኃብቶች እና አገልግሎቶች ዕኩል ዕድሎች የሚሰጥ፣ ለግልጽነት እና ቀጣይነት ያለውን መሻሻል ለማረጋገጥ ማስረጃ የሚጠቀም እንዲሁም ከመድልዖ እና ትንኮሳ ነጻ የሆነ መንግሥት እንዲኖር ቁርጠኛ አቋም አላቸው፡፡

መኖሪያ ቤት እንደ መብት

ኤሪን መኖሪያ ቤት ማግኘት ሰብዓዊ መብት ነው፤ ጠንካራ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ ማኅበረሰቦች ሁላችንንም ይጠቅማሉ ብለው ያምናሉ፡፡ የምክር ቤት ሊቀመንበር ሲሆኑ፣ ያሉንን ግብዓቶች ሁሉ አቅምን ያገናዘቡ መኖሪያ ቤቶችን ተደራሽነት ለማስቀጠል እና ለማሻሻል እንዲውሉ እና የቤት ባለቤትነትን ለማረጋገጥ ያላሰለሰ ጫና ያሳድራሉ፡፡

ሁኔታዎችን እንደ አግባብነቱ የምታስተናግድ ከተማ እና ቀጣይ የወደፊት ሁኔታ

ያለፉት ሁለት ዓመታት ያሳዩን ነገር ቢኖር፣ ሕይወታችን በቀላሉ ሊመሳቀል የሚችል መሆኑን ነው፡፡ የምክር ቤት ሊቀመንበር በሚሆኑ ጊዜ ኤሪን የሚመሩትን ምክር ቤት ማኅበረሰባችንን ለማጠናከር እና መሠረተ ልማቶቻችንን ለማሻሻል ይጠቀሙበታል፤ የሚፈጸሙትም ሁሉ በመንገዳችን የሚገጥመን ምንም ቢሆን ብሩህ እና ቀጣይነት ያለውን የወደፊት ጉዞ በማረጋገጥ ራዕይ ይሆናል፡፡

ስኬታማ ቤተሰቦች

ኤሪን ቤተሰብን መደገፍ ብዙ የሚጠይቅ እንደሆነ ያውቃሉ፤ የምክር ቤቱ ሊቀመንበር በሚሆኑ ጊዜ ለዲሲ ቤተሰቦች ቅድሚያ የሚሰጥ መንግሥት ይመራሉ (በሕይወት ዓይነት ወይም ደረጃ ምንም ቢሆን)፡፡

በሥራ ላይ ባሉ ሰዎች እና በአነስተኛ የንግድ ሥራዎች ላይ ኢንቬስት ማድረግ

ከተማችን የምርጫ ቅስቀሳ የገንዘብ እርዳታዎችን ለሚሰበስቡ ወይም ሎቢስቶችን ለሚቀጥሩ ብቻ ሳይሆን ለሁላችን መሥራት አለባት፡፡ የምክር ቤት ሊቀመንበር እንደመሆናቸው መጠን፣ ኤሪን ከዲሲ ሠራተኛ ነዋሪዎች ማለትም ከጎረቤቶቻችን፣ ከቤተሰባችን እና ከጓደኞቻችን ጋር ይቆማሉ፤ በዚህም ለመደበኛው ሰው የመጫወቻውን ሜዳ ያደላድላሉ ማለት ነው፡፡

በርካታ ወሳኝ ጉዳዮች እንዳሉ እና መንግሥትም የእያንዳንዱን ወገን ፍላጎት ለማሟላት ሁሌም መሻሻል እንደሚችል እናውቃለን፡፡ ለኤሪን በ erin@erinfordc.com.