በሥራ ላይ ባሉ ሰዎች እና በአነስተኛ የንግድ ሥራዎች ላይ ኢንቬስት ማድረግ

ከተማችን የምርጫ ቅስቀሳ እርዳታ ለሚሰበስቡ እና ለሎቢስቶች ብቻ ሳይሆን ለሁላችንም መሆን አለባት፡፡ ነገር ግን አነስተኛ የንግድ ሥራዎች እና የሠራተኛ መደብ ሰዎች ሲቸገሩ እና በኢኮኖሚ ዕኩልነት ዕጦት እና በኑሮ ውድነት ምክንያት ከዲሲ እንዲወጡ ሲገፉ እንመለከታለን፡፡ የኢኮኖሚ እኩልነት እጦት ከሌሎች ይልቅ በጥቁር እና ሂስፓኒክ የዋሽንግተን ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ሲያስከትል እናያለን፡፡ የምክር ቤት ሊቀመንበር ሲሆኑ ኤሪን የጨዋታ ሜዳው ለሁሉም ሰው እኩል እንዲሆን ከዲሲ ሠራተኛ ሰዎች ማለትም ከጎረቤቶቻችን፣ ከቤተሰቦች እና ከጓደኞቻችን ጋር ይቆማሉ፡፡

ኤሪን እያንዳንዱ በዲሲ ያለ ሰው ጥሩ ሥራ ሊያገኝ ይባል ብለው ያምናሉ፡፡ በታሪክ ብቸኛው የጥቁሮች ዩኒቨርሲቲ በሆነው በኮሎምቢያ ዲስትሪክት ዩኒቨርሲቲ እና በሥራ ሥልጠና ፕሮግራሞች ላይ ኢንቬስት ማድረግ የተሻሉ ዕድሎን ለብዙዎች ሰዎች ይፈጥራል፡፡ የአገባቢ አስተዳደራችን ሥራ ከጥሩ ክፍያ ጋር፣ አስፈላጊ በሚሆን ጊዜ ዕረፍት ከክፍያ ጋር እና የጤና አገልግሎት ተደራሽነትን ማረጋገጥ ይችላል፡፡ የኢሚግሬሽን ሁኔታ ምንም ቢሆን የዋሽንግተን ነዋሪዎች ሥራ እና ገቢ ማግኘት አለባቸው፡፡ ኤሪን በሥራ ዘመናቸው ሁሉ የሥራ ቦታዎች ደህንነታቸው የተጠበቀ፣ ከመድልዖ እና ትንኮሳ ነጻ እንዲሆኑ ችግሮች በሚኖሩ ጊዜ ደግሞ የበቀል እርምጃ ይደርስብኛል ከሚል ፍርሃት ነጻ በሆነ መልኩ የመናገር መብት እንዲኖር ሲሰሩ ቆይተዋል፤ ሊቀመንበር ሲሆኑ ደግሞ በዚሁ ሥራ ይቀጥሉበታል፡፡

አነስተኛ ንግዶች የመኖሪያ አካባቢዎቻችን ማዕከላት ናቸው፡፡ ነገር ግን ፍላጎቶቻቸውን በሚያሟላ መልኩ ተጨማሪ እገዛ ያሻቸዋል፡፡ ይህም ማለት ከትልልቅ ገንቢዎች እና ከድንበር ዘለል ኮርፖሬሽኖች ይልቅ በግብር ማነቃቂያዎች ላይ ትኩረት ማድረግ ማለት ነው፡፡ ኤሪን ሜን ስትሪትስ ፕሮግራም ምን ያህል ውጤታማ ሊሆን እንደሚችል በተግባር ያውቃሉ፡፡ ነገር ግን ሁሉም የመኖሪያ አካባቢዎች እኩል ተጠቃሚነት ይኖራቸዋል ማለት አይደለም፤ ስለዚህ እኩል ፈንድ እንዲመደብ ይታገላሉ፡፡ አሁን ያሉ ምግብ አቅራቢዎች ጤናማ ምግብ እና ሥዎችን ለሚፈልጓቸው የማኅበረሰባችን ክፍሎች ለማቅረብ በበቂ ያልሰሩትን ማሻሻል ያስፈልጋል ብለው በጽኑ ያምናሉ፡፡ በጋራ በመሆን የዲሲ መንግሥት ባለጠጎች የሆኑትን ከመደጎም ይልቅ ሰፊ በቤት ላይ የተመሠረተ ስኬትን መደገፍ ላይ ተኩረት ማድረግ ይችላል፡፡

የወቅቱ ሊቀመንበር ከሰዎች ይልቅ ለመኖሪያ አካባቢዎቻችን ከፍ ያለ ደመወዝ እንዲከፈል የቀረበውን የዲሲ መራጮችን ፈቃድ ውድቅ ለማድረግ የሚደረገውን ጥረት ከሚመሩ፣ ለእለት ተዕለት ሠራተኞች ሰፊ የግብር እፎይታ እንዳይሰጥ ከሚታገሉት እና እርስ በእርስ ለተያያዙ ዲቨሎፐሮች የሚሰጡ ድጎማዎችን ለማስጸደቅ ከትልልቅ የንግድ ድርጅቶች እና ሎቢስቶች ጎን ቆመዋል፡፡ አሁን ጊዜው የአዲስ አመራር ነው፤ ኤሪን ለዲሲ ሠራተኞች እና ለአካባቢያችን አነስተኛ ንግዶች መታገላቸውን ይቀጥላሉ፡፡

የኤሪን ተሞክሮ ፡-

ኤሪን በኦል ታኮማ ቢዝነስ አሶስዬሽን (ሜን ስትሪት ታኮማ) ቦርድ ውስጥ በማገልገል ላይ ሲሆኑ፣ አፕታውን ሜን ስትሪትን ወደ ኬኔዲ ስትሪት፣ ኖርዝ ዌስት ለማምጣተ የሚደረገው ጥረት አካል ነበሩ፡፡ ሥራ አስፈጻሚ ዳይሬክተሮች ለተጨማሪ ጊዜ እንዲቆዩ ለአካካቢ አነስተኛ የንግድ ድርጅቶች በሚሰጡት ድጋፍ እንዲቀጥሉበት ተጨማሪ የሜን ስትሪት ፈንዲንግ እንዲሰጥ ተሟግተዋል፡፡ በዲሲ የሚገኙ የቲፕ ሠራተኞች ንዑስ አነስተኛ የደመወዝ መጠን እንዲጨምር እና ሕጋዊ ሰነድ የሌላቸውን ጨምሮ የኮቪድ-19 እገዛ ለሁሉም ሠራተኞች እንዲሰጥ ጠንካራ ድጋፍ አድገዋል፡፡