መኖሪያ ቤት እንደ መብት

ሁሉም የዲሲ ነዋሪዎች ደህንነቱ የተጠበቀ፣ የተረጋጋ እና የተረጋገጠ መኖሪያ ቤት ሊኖራቸው ይገባል፡፡ ሆኖም ግን በቤት እልባዎች መቆያዎች መጨመር፣ እየተበላሹ ባሉት የሕዝብ መኖሪያ ቤቶች አቅርቦት ላይ ስር የሰደደ የኢንቬስትመንት እጥረት፣ ነዋሪዎች ማኅበረሰቦቻቸውን ጥለው እንዲሄዱ የሚያስገድድ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ እና ለሠራተኛው መደብ ሰዎች ሊደረስበት የማይችል ከተማ መሆኑ እየተባባሰ መምጣቱን እንመለከታለን፡፡ ኤሪን የምክር ቤቱ ሊቀመንበር ሲሆኑ መኖሪያ ቤቶች አቅርቦት እና ባለቤትነት በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ እንዲሆን ያላሰለሰ ግፊት ያደርጋሉ፤ ያለውን ዘዴ ሁሉ ይጠቀማሉ፡፡

ኤሪን መኖሪያ ቤት ሰብዓዊ መብት እንደሆነ እና ጠንካራ እና ደህንነታቸው የተጠበቀ ማኅበረሰቦች ሁላችንንም እንደሚጠቅሙን ያምናሉ፡፡ እያንዳንዱ የዲሲ ነዋሪ የመኖሪያ ቤት የማግኘት ክብር እንዲኖረው ምክር ቤቱ ገንዘብ እንዲመድብ እና ቅድሚያ ሰጥቶ ሕግ እንዲያወጣ የመሪነት ሚናቸውን ይጫወታሉ፡፡ በዚህም የሚከተሉት ይካተታሉ፡-

  • ቤት አልባነትን ማስቀረት
  • በዲሲ የመጠለያ ሥርዓት ማሻሻያዎች ላይ ኢንቬስት ማድረግ 
  • ለሕዝብ መኖሪያ ቤቶች ጥበቃ እና ዕድሳት ማድረግ
  • Preventing discrimination, harassment, and other barriers for LGBTQ+ neighbors in accessing programs and services
  • ተግዳሮት ወይም ያልታሰበ የገንዘብ ቀውስ ለሚገጥማቸው ተከራዮች እና የቤት ባለቤቶች ድጋፍ መስጠት
  • የኪራይ ቁጥጥርን ማጠናከር እና ማስፋፋት
  • ለዝቅተኛ፣ መካከለኛ እና ቁርጥ ገቢ ላላቸው ነዋሪዎች የቤት ገዢ እገዛ መስጠት 
  • ለረጅም ጊዜ እና ለአዲስ ነዋሪዎች አዲስ የመኖሪያ ቤቶች አማራጭን መደገፍ 
  • ይበልጥ በጥልቀት በተመጣጣኝ ወጋ የመኖሪያ ቤት አማራቾችን ማቅረብ 

በተጨማሪም፣ ኤሪን በተመጣጣኝ ዋጋ ለሚቀርቡ መኖሪያ ቤቶች ለምሳሌ ማኅበራዊ መኖሪያ ቤት እና የማኅበረሰብ የመሬት ትረስት አዳዲስ ሞዴሎች ይጠቀማሉ፡፡ ይህም መኖሪያ ቤቶች በይበልጥ በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲገኙ ከማድረጉም ባሻገር ብዝሃነት ያላቸው፣ አካታች እና አቅማቸው የተገነባ ማኅበረሰቦች እንዲኖሩን ያደርጋል፡፡ 

ጥረቱ በጀት በመፍቀድ ወይም ሕግ በማውጣት አያበቃም፤ ኤሪን ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ያላሰለሰ ቁጥጥር የማድረግ ክህሎቶች አሏቸው፤ ገንዘብ በተገቢው መንገድ ወጪ መደረጉን እና ኤጀንሲዎችም ሕጎችን እና ደንቦችን ማክበራቸውን ያረጋግጣሉ፡፡ ጠንካራ ቁጥጥር አለመኖሩ ከዋነኛ የተመጣጣኝ መኖሪያ ቤቶች አቅርቦት ዘዴዎች መካከል አንዱ የሆነው የሃውሲንግ ፕሮዳክሽን ትረስት ፈንድ የመኖሪያ ቤት እጅግ ለሚያስፈልጋቸው እንኳን መኖሪያ ቤት ለማቅረብ መስፈርቶችን በቀጣይነት ማሟላት እንዳይችል አድርጓል፡፡ የገንዘብ አወጣጣችን አግባብነት የጎደለው በመሆኑ በተደጋጋሚ የፌዴራል መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ እንዳይደርሰን ምክንያት ሆኗል፡፡ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ነዋሪዎች በመንግሥት የሚቀርብ ቤት ለማግኘት በመጠበቅ ላይ ናቸው፤ ነገር ግን ወረፋ የያዙ ሰዎች ዝርዝር ባለበት እንደቆመ ነው፡፡ ተቆጣጣሪ ኤጀንሲዎቻችን ሥራቸውን ለመስራት ባለመቻላቸው እና ቁጥጥር ባለመኖሩ ምክንያት ነዋሪዎች በአስቸጋሪ እና ፈጽሞ ለኑሮ በማያመቹ ሁኔታዎች ውስጥ እንዲገኙ አድርጓል፡፡ ኤሪን ቁጥጥርን ብቻ ሳይሆን በፖሊሲዎቻችን ቅድሚያ የተሰጣቸው ጉዳዮች እውን እንዲሆኑ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥተው ይሰራሉ፡፡ 

አሁን ያሉት የምክር ቤቱ ሊቀመንበር ፖለቲካ የጀመሩት በዲሲ የባለጠጎች መኖሪያ ሰፈሮች አዳዲስ የመኖሪያ አካባቢዎች ማየት እንደማይፈልጉ በመግለጽ ነበር፡፡ የዲሲ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤት የማግኘት ክብር እንዲኖራቸው ማድረግ የመኖሪያ አካባቢዎቻችንን እና ከተማውን ያጠነክራል፤ ብዝሃነት ያላትን፣ አካታች እና ንቁ ዲሲ እውን ያደርጋል፡፡ ኤሪን ሁሉም ሰው በማኅበረሰቦቻችንን መልካም ተቀባይነት እንዲኖረው ለማረጋገጥ በሕዝብ አገልግሎት ጊዜያቸውን የገነቡ ሰው ናቸው፡፡

የኤሪን ተሞክሮ ፡-

ኤሪን ስር የሰደደ መኖሪያ ቤት አልባነትን ለማስቀረት እና እያንዳንዱም ሰው የመኖሪያ ቤት ክብር እንዲኖረው ሙሉ የገንዘብ አቅርቦት እንዲኖር ሳያቋርጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ የዲሲ አጠቃላይ ዕቅድ መኖሪያ ቤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ መገኘትን እና የሕዝብ መኖሪያ ቤቶችን መጠበቅ እና ማቆየት አስፈላጊ እንደሆነ አበክሮ ለማሳሰብ አድቫይዘሪ ኔበርሁድ ኮሚሽን ጫና የማሳደር ጥረቱን መርተዋል፡፡ በኤሪን አመራር ስር፣ አድቫይዘሪ ኔበርሁድ ኮሚሽን ለመጀመሪያ ጊዜ የመኖሪያ ቤት ፍትሕ ኮሚቴ ወይም ሃውሲንግ ጀስቲስ ኮሚቴ ፈጥሯል፤ በመኖሪያ አካባቢውም በመቶዎች የሚቆጠሩ በተመጣጣኝ ዋጋ የሚቀርቡ ቤቶች እንዲጠበቁ፣ እንዲገቡ አድርጓል፤ ሌሎችም በሂደት ላይ ናቸው፡፡