ሥነ ምግባር የተመላ እና ተጠያቂ መንግሥት

ሁሉም የዲሲ ነዋሪዎች የሚወከሉት መንግሥትን ተጠያቂ በሚያደርጉ ሰዎች ነው፡፡ ብዙ ጊዜ ተመራጭ ባለሥልጣኖች ሥልጣናቸውን እና የሚያገኙትን ልዩ መብት ለራሳቸው ሲጠቀሙበት እና ማኅበረሰቦቻችንን ማገልገል ሳይችሉ እናያቸዋለን፡፡ በዲሲ የፍተሐዊ ምርጫዎች ፕሮግራም ተካፋይ እና ራሳቸውን ለሕዝብ አገልግሎት እንደሰጡ እና በተቋም ተጠያቂነት ላይ ጥልቅ ሙያዊ ተሞክሮ እንዳለው ሰው፣ ኤሪን ለዲሲ ለመልካም አስተዳደር አዲስ ራዕይ ይዘው ይመጣሉ፡፡

ኤሪን በዲሲ ፍትሐዊ ምርጫ ፕሮግራም ይሳተፋሉ፤ ይህ ፕሮግራም ብቁነቱ ላላቸው እጩዎች የተወሰነ ፐብሊክ ማቺንግ ፈንድ የሚሰጥ የምርጫ ቅስቀሳ የፋይናንስ አቅርቦት ፕሮግራም ነው፡፡ የድርጅት እና የፖለቲካ እርምጃ ኮሚቴ እርዳታዎችን በማጣመር ተጠሪነታቸው እና አብረውም የሚሰሩት ከነዋሪዎች ጋር እንጂ ከሎቢስቶች ጋር አይደለም፡፡ የድርጅት ረጂዎች ጋር ግንኙነት የሌላቸው የልጆች እናት ኤሪን፣ ጥቅም ካላቸው ቡድኖች እስከ አሁን በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ገንዘብ ለማሰባሰብ ከቻሉት እና ለረጅም ጊዜ በሥልጣን ላይ ከቆዩት ሰው ጋር ለመወዳደር የሚያስችላቸው ነው፡፡ የፍትሐዊ ምርጫዎች ፕሮግራም (ፌር ኢሌክሽንስ ፕሮግራም) እንዲጸድቅ ድጋፋቸውን የሰጡበት ምክንያት መደበኛ የዲሲ ነዋሪዎች ድምጻቸው መሰማት እንዲችል ነው፡፡

የዲሲ ምክር ቤት ካላቸው ወሳኝ ሚናዎች መካከል አንዱ ክትትል ነው፤ የቁጥጥር አካል ተደርጎ ሊወሰድ የሚችለው ደግሞ ፕሮገራሞች እና የከተማ አገልግሎቶች ለነዋሪዎች በቀላሉ ተደራሽ እንዲሆኑ ማድረግ እና የመንግሥት ኤጀንሲዎች እነዚህን ፕሮግራሞች በጥሩ ሁኔታ እና በውጤታማነት እንዲተገብሩ ማድረግ ነው፡፡ የቁጥጥሩ ሂደት የሚያበቃው ምክር ቤቱ ሕግ ሲያወጣ አይደለም፤ ይልቁንም ሕጉ በሚገባ ተግባራዊ እንዲሆን እና ወደ እውነታነት እንዲመጣ ቀጣይነት ያለው ሥራ ይፈልጋል፡፡ የምክር ቤት ሊቀመንበር እንደመሆናቸው መጠን ኤሪን ምክር ቤቱ መንግሥታችን ውጤታማ እንዲሆን እያንዳንዱን የቁጥጥር ዘዴ ማለትም የዲሲ ኦዲተር መሥሪያ ቤት የኤጀንሲዎችን እና ፕሮግራሞችን ውጤታማነት ለመቆጣጠር እንዲችል ማስፋት፣ ሕጎቻችን ስትራቴጂያዊ እና ውጤታማ እንዲሁም የምክር ቤቱ አባላት ውጤታማ ያልሆኑ ኤጀንሲዎች ተጠርተው ለጥያቄዎች ምላሽ እንዲሰጡ የማዘዝ ሥልጣን እንዲኖራቸው ራሱን የቻለ የሕግ አውጪ የምርምር ኤጀንሲ መመስረት ተፈጻሚ እንዲሆኑ ይሰራሉ፡፡

ምክር ቤቱም ራሱ አባላቱን ተጠያቂ ማድረግ መቻል አለበት፡፡ ሊቀመንበር እንደመሆናቸው መጠን ኤሪን የምክር ቤት አባላት ሥነ ምግባር መላበሳቸውን እና ምክር ቤቱም በጋራ መሥራቱን፣ በጋራ ውሳኔ አሰጣጥ እንደሚሳተፍ እና የአገር ውስጥ ተቋማትን እና መርሆችን ማክበሩን ያረጋግጣሉ፡፡ ሥልጣን በአንድ ሰው እጅ ውስጥ በሚከማች ጊዜ ምክር ቤቱ በአግባቡ መሥራት አይችልም፡፡

የኤሪን ተሞክሮ ፡-

ኤሪን በወቅቱ የዋርድ 2 የምክር ቤት አባል የነበሩት ጃክ ኤቫንስ ለፈጸሙት የሥነ ምግባር ጉድለት ተጠያቂ እንደሆኑ ምክር ቤቱ እርምጃ እንዲወስድ የቀረበውን ጥያቄ መርተዋል፤ ይህም በመጨረሻ ምክር ቤቱ ምርመራ እንዲያደርግ እና ኤቫንስም ከኃላፊነታቸው እንዲወርዱ አድርጓል፡፡ ኤሪን የመንግሥታችንን ተደራሽነት እና ብቁነት ለማሻሻል ጥረት አድርገዋል፤ ከጥረቶቻቸውም መካከል የመንግሥት ስብሰባዎችን ተደራሽነት ለማረጋገጥ በመላው ከተማ የተደረጉ ጥረቶችን መምራት፣ በጠንካራ እና በአስተማማኝ በፖስታ ድምጽ የመስጠት አሰራር መሠረት ምርጫን የተሻለ እና ቀላል ማድረግ እና ለተመራጭ ባለሥልጣናት ልዩ ጥቅማ ጥቅሞች እንዲቀሩ ማድረግ፡፡