የማኅበረሰብ ደህንነት

በማኅበረሰቦቻችን ውስጥ ያለውን የኃይል ድርጊት ለማስቆም ፈጣን መፍትሔ የለም፡፡ ጉዳት የደረሰበት ሰው ሁሉ የቤተሰባችን አባል፣ ጓደኛችን እና ጎረቤታችን ነው/ናት፤ በዚህ ምክንያት በኃይል ሥራ ሚደርስ ጉዳት ሁላችንም ላይ ተጽዕኖ ያስከትላል፡፡ የኃይል ድርጊት ለአሥርተ ዓመታት የቆየ ውዝፍ ያልተሰራ ሥራ ውጤት በመሆኑ በርካታ የመኖሪያ አካባቢዎችን ያፍረከረከውን ቁስል ለማዳን ቀጣይነት ያለው እና በዕቅድ የሚመራ ተግባር ይፈልጋል፡፡ በአገር ደረጃ ቀደምትነት ከሚሰጣቸው ጉዳዮች እና ምርጥ አሰራሮች ጋር በተጣጣመ ሁኔታ፣ ኤሪን የኃይል ድርጊትን ለመቀነስ እና ተጽዕኖውን ለማሳነስ፣ የኃይል ድርጊት በማስቀረት ላይ ኢንቬስት ለማድረግ እና ጠንካራ ማኅረሰቦችን ለመገንባት ቁርጠኛ አቋም አላቸው፡፡

የምክር ቤት ሊቀመንበር በሚሆኑ ጊዜ፣ ኤሪን ለአጠቃላይ፣ ለመላው ከተማ የኃይል ድርጊት የመከላከል ዕቅድ ድጋፍ ይሰጣሉ፡፡ ይህም ከዚህ የሚከተሉትን ያካትታል፡- 

  • ዕድሎችን ለመፍጠር፣ በተለይ ደግሞ ለተመላሽ ዜጎች እና ወጣቶች ዕድል ለመስጠት በሥራዎች፣ በፕሮግራም፣ እና በመዝናኛዎች ላይ ትርጉም ባለው መልኩ ኢንቬስት ማድረግ፤ ለምሳሌ በኔበርሁድ ሴፍቲ ኤንድ ኢንጌጅመንት መሥሪያ ቤት የፓዝዌይ ፕሮግራም እና ሰመር ዩዝ ኢምፕሎይመንት ፕሮግራም፤
  • በወረርሺኝ ደረጃ ካለው በጦር መሣሪያ የሚፈጸሙ የኃይል ድርጊቶች ክስተት ጋር የሚመጣጠኑ፣ የተቀናጁ፣ በማስረጃ ላይ የተመሠረቱ፣ ግልጽ እና በሚገባ የገንዘብ ድጋፍ የሚደረግላቸው የኃይል ድርጊት መከላከያ ፕሮግራሞች፣ የኃይል ድርጊት ከመጨመሩ በፊት ለመኖሪያ አካባቢዎች መድረስ እና የፕሮግራሞችን ምዘና እና በእነርሱም ላይ የሚደረጉ ማሻሻያዎችን መፍቀድ፤
  • ጠንካራ ስለ ድንገተኛ አደጋ በመረጃ ላይ የተመሰረቱ አገልግሎቶች በተለይ ደግሞ ለሕጻናት፣ ለወጣቶች፣ በኃይል ድርጊት ተጽዕኖ ስር ለወደቁ ማኅበረሰቦች እና በኃይል ድርጊት መከላከል የመስክ ሥራ ላይ ለተሰማሩ ሰዎች፡፡
  • Collaborative efforts to prevent and address hate crimes that are done with sensitivity to populations that are historically over-policed and often struggle in interactions with law enforcement

እንዲሁም የኃይል ድርጊትን መከላከል ማለት ሕገወጥ መሣሪዎችን ከየመንገዱ ማስወገድ፣ የጦር መሣሪያ እና የጥይቶች አምራቾችን እንዲሁም አከፋፋዮችን ተጠያቂ ማድረግ ማለትም ነው፡፡ ይህም የኃላፊነት ወሰን ተሻጋሪ ጥረትን እንደሁም ግልጽ፣ ሥነ ምግባር የተላበሰ እና ተጠያቂ የፖሊስ መምሪያን የሚጠይቅ ሥራ እንደሆነ ኤሪን ይገነዘባሉ፡፡

ከፍተኛ የሆነ የኢንቬስትመንት ዕጥረት የሚገጥማቸው ማኅበረሰቦች ከፍተኛ የኃይል ድርጊት ሰለባ ይሆናሉ፡፡ እያንዳንዱ የዲሲ ካርታ ተመሳሳይ የዘር፣ የማኅበራዊ -ኤኮኖሚያዊ እና የመልክዓ ምድራዊ ልዩነት ማለትም ሞትን ያስከተሉ የትራፊክ አደጋዎች፣ የኮቪድ-19 የክትባት ምጣኔዎች እና ሞት፣ የጤናማ ምግብ እጥረት፣ የተጎሳቆሉ እና ወና ቤቶች፣ የኢንተርኔት ተደራሽነት፣ የወላድ ሞት፣ ወንጀል ወይም ማናቸውም የሌሎች ጉዳዮችን ስርጭት ያሳያሉ፡፡ እነዚህ ልዩነቶች በታሪክ የተለያዩ የመኖሪያ አካባቢዎች እና በጥቁር የዋሽንግተን ነዋሪዎች መካከል ለአስረተ ዓመታት የዘለቀ ስር የሰደደ የኢንቬስትመንት እጥረት ውጤት ናቸው፡፡ ያለ ትኩረት፣ የመኖሪያ አካባቢዎቻችንን መከፋፈላቸውን ይቀጥላሉ፡፡ 

ኤሪን አስቀድሞ ለታቀደ የመሠረተ ልማት ሥራ ለምሳሌ ለመንገዶች እና ደህንነቱ ለተጠመቀ መተላለፊያ፣ የተዋቡ መጫወቻ ስፍራዎች፣ ፓርኮች እና አረንጓዴ ስፍራዎች፣ አስተማማኝ የቆሻሻ አያያዝ፣ ለንጹህ የመኖሪያ አካባቢዎች እና ጠንካራ የሕዝብ ትራንስፖርት፣ በታሪክ የነበረውንም ትኩረት ያለመስጠት ሁኔታ ለማስተካከል ቀጣይነት ባለው መልኩ ከነዋሪዎች ጋር አብሮ መስራት ያስፈልጋል፡፡ የመንግሥት አገልግሎቶች ቀጣይነት እና ከፍተኛ ጥራት እንዲኖራቸው፣ ኤሪን እነዚህ ልዩነቶች ማስተካከል እንደሚቻል እና የመኖሪያ አካባቢዎቻችን ለሁሉም ሰው የተሻሉ ለማድረግ እንደሚያግዙ ያውቃሉ፡፡

የኤሪን ተሞክሮ ፡-

ኤሪን ከሕዝብ ጤና አንጻር ለወንጀል መፍትሔ ለመስጠት የኃይል ድርጊትን በመከላከል ላይ ኢንቬስት ማድረግ ይገባል በሚል ቀጣይነት ባለው መልኩ ድጋፍ ሲሰጡ ቆይተዋል፤ ሁሉንም የሕዝብ ደህንነት ኤጀንሲዎች ቁጥጥር፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት ሰርተዋል፡፡ ኤሪን 311 ሱፐር ተጠቃሚ ናቸው፡፡ ነገር ግን 311 ጥያቄዎች ማቅረብ ብቻ ሳይሆን ሥርዓታዊ የሆኑ ጉዳዮችን ይለያሉ እንዲሁም የትራፊክ ደህንነትን፣ ይበልጥ አስተማማኝ እና ተደራሽ የሕዝብ ትራንስፖርት ወይም ይበልጥ መደበኛ የቆሻሻ አሰባሰብን በተመለከተ ለውጦች እንዲደረጉ ይገፋፋሉ፡፡