ኤሪን ፓልመር፣ ዴሞክራት ለዲሲ ምክር ቤት ሊቀመንበር

አሁን የአዲስ አመራር እና ለዲሲ የተሻለ ብሩህ ራዕይ የምንሰንቅበት ጊዜ ነው፡፡

ኤሪን ይተዋወቁ

ኤሪን ፓልመር እባላለሁ፤ የሦስት ብሩካን ልጆች እናት ነኝ፤ የሥነ ምግባር ጠበቃ ስሆን፣ ራሴን ለሕዝብ አገልግሎት የሰጠሁ ሰው ነኝ፡፡ ከሞላ ጎደል ከሁለት አስርተ ዓመታት በፊት ወደ ዲሲ ከተዘዋወርኩ ጊዜ ጀምሮ፣ በፌዴራል እና በአካባቢ መንግሥታት ዘንድ የሥራ ቦታ ጥበቃዎችን በማስፋፋት ስሰራ እና ለግልጽነት እና ተጠያቂነት ስታገል ቆይቻለሁ፡፡ በዋርድ 4 አድቫይዘሪ ኔበርሁድ ኮሚሽነር እንደመሆኔ መጠን ፣ በዕለት ተዕለት ኑሯችን ላይ ተጽዕኖ ስላላቸው ጉዳዮች ማለትም እንደ ትራፊክ ደህንነት፣ ከፍተኛ ጥራት ያላቸው ትምህርት ቤቶች፣ እና የተሻለ የሕዝብ ትራንስፖርት በተመለከተ ከጎረቤቶቼ ጋር በመሆን እታገላለሁ፡፡ ወደ ዲሲ ምክር ቤት አዲስ ኃይል እና ራዕይ ለማምጣት ለሊቀመንበር ወንበር በመወዳደር ላይ ነኝ፡፡

ከዲሲ ነዋሪዎች የሚገኙ እገዛዎች በዲሲ ፍትሐዊ ምርጫ ፕሮግራም 5x ይጣመራሉ!

ወደ $60 ይቀየራል

ወደ $300 ይቀየራል

ወደ $600 ይቀየራል

ወደ $1,200 ይቀየራል

Erin is the only Democrat for Council Chair using DC’s Fair Elections program, which means she’s rejecting corporate donations and is accountable to DC residents.

የእኛ የፖሊሲ አጀንዳ

ኤሪን መሠረታዊ ፍላጎቶችን ማለትም መኖሪያ ቤት፣ ትምህርት እና የጤና አገልግሎትን እንደ መብት በመቁጠር ኢንቬስት የሚያደርግ እና በዚህም የዲሲ ነዋሪዎች እና ቤተሰቦች ስኬታማ እንዲሆኑ የሚሰራ የዲስትሪከት አስተዳደር እንዲኖር በቁርጠኝነት ይሰራሉ፡፡ ሁሉም ሰው ደህንነቱ ለተጠበቀ እና ጤናማ ማኅበረሰብ የሚያስፈልግ ከፍተኛ ጥራት ያለው፣ አስተማማኝ የመንግሥት አገልግሎት የማግኘት መብት አለው ብለው ይምናሉ፡፡

የምወዳደርበት ምክንያት

ቀጣይዋ የዲሲ ምክር ቤት ሊቀመንበር ለመሆን የምወዳደርበት ምክንያት አሁን ከማናቸውም ጊዜ ይልቅ በመላው ዲሲ ለእያንዳንዱ ሰው እና ቤተሰብ የሚሰራ አመራር ስለሚያስፈልገን ነው፡፡ መንግሥት የዛሬዎቹን ተግዳሮቶች ፊት ለፊት እንዲገጥም እና ለተሻለ ነገ የሚያስፈልግ መሠረተ ልማት እንዲገነባ ሪፎርም ለማምጣት ቁርጠኛ አቋም አለኝ፡፡ መንግሥት ሁሉንም ነዋሪዎች እንዲያገለግል እና ዲሲን ይበልጥ ጠንካራ እንዲያደርግ ለዓመታት ለሥነ ምግባር እና የተሻለ ተጠያቂነት ስታገል ያካበትኩትን ልምድ ወደ ዊልሰን ሕንጻ አመጣለሁ፡፡ በአዳዲስ ሃሳቦች፣ በትብብር አመራር እና ጠንካራ እሴቶች እያንዳንዱ የዋሽንግተን ነዋሪ ብሩህ የወደፊት ጊዜ እንደሚኖረው ማረጋገጥ እንችላለን፡፡